ለሮሒንግያ ሙስሊሞች ቀውስ መፍትሔ ለማፈላለግ ትናንት ሰኞ ሚያንማር የገቡት የሮማው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት አባ ፍራንሲስ፣ ከአገሪቱ የሲቪል መሪ ኡን ሳን ሱ ቺ ጋር ተገናኝተው ባደረጉት ንግግር፣ የሮሒንግያን ቀውስ ሳያነሱ ባጠቃላይ የአንድነት ጥሪ ማሰማታቸው ተገለጸ።
ዋሺንግተን ዲሲ —
ለሮሒንግያሙስሊሞች ቀውስ መፍትሔ ለማፈላለግ ትናንት ሰኞ ሚያንማር የገቡት የሮማው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት አባ ፍራንሲስ፣ ከአገሪቱ የሲቪል መሪ ኡን ሳን ሱ ቺ ጋር ተገናኝተው ባደረጉት ንግግር፣ የሮሒንግያን ቀውስ ሳያነሱ ባጠቃላይ የአንድነት ጥሪ ማሰማታቸው ተገለጸ።
የሰብዓዊ መብት ጥበቃና ፍትህ መከበር እንዳለባቸው ያሳሰቡት አባ ፍራንሲስ፣ ቀውሱን ከማስወገድ አኳያ ሃይማኖት ጠቃሚ ሚና ሊጫወት እንደሚችልም አመልክተዋል።
“አመጣጤ፣ የእርቅና የሰላም መልዕክት ያለበትን የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ለማወጅ ነው” ሲሉ ትናንት በቫቲካን ራድዮ የተናገሩት አባ ፍራንሲስ፣ የሮሒንግያ ሙስሊም ፍልሰተኞች የተሰደዱበትን ባንግዳላዴሽን ባለፈው ሐሙስ መጎብኘታቸውም ይታወቃል።