የድጋፍ ሰልፍ ላይ የደረሰውን አደጋ ሀገራት አወገዙ

  • ቪኦኤ ዜና
የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር አብይ አሕመድ

የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር አብይ አሕመድ

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ላመጡት ለውጥ በተጠራ የድጋፍ ሰልፍ ላይ የደረሰውን አደጋ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ የአፍሪካ ሕብረትና ሀገራት እንዳወገዙት የኢትዮጵያ ብሮድካስቲግ ኮርፖሬሽን ዘግቧል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ላመጡት ለውጥ በተጠራ የድጋፍ ሰልፍ ላይ የደረሰውን አደጋ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ የአፍሪካ ሕብረትና ሀገራት እንዳወገዙት የኢትዮጵያ ብሮድካስቲግ ኮርፖሬሽን ዘግቧል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬሽ በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ የተፈፀመው ድርጊት አስነዋሪና አሳሳቢ ነው ማለታቸውን ገልጿል፡፡ ዋና ፀሀፊው ለተጎጂዎችና ለቤተሰቦቻቸው መፅናናትና ቶሎ እንዲያገግሙ መልካም ምኞተያቸውን ገልፅዋል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከኢትዮጵያ ህዝብና መንግሥት ጋር እንደሚቆም ዋና ፀሀፊው በቃል አቀባያቸው በኩል መናገራቸውን የድርጅቱ ዜና ማዕከል መዘገቡን የኢትዮጵያ ብሮድካስትሪንግ ኮርፖሬሽን ጠቁሟል።

የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪህም አደጋውን አውግዘዋል፡፡ የተባበሩት አረብ ኤምሬትቶች በሰልፈኞች ላይ ቦንብ ተወርውሮ ለሁለት ሰው ሞትና ለ164 ሰው መቁሰል ምክንያት የሆነውን ድርጊት በፅኑ እንደምታወግዘው አስታውቃች፡፡

ኦማንም ድርጊቱን በፅኑ እንደምታወግዘው በውጭ ጉዳይ ሚንስትሯ በኩል መግለጿን ሞስካት ደይሊ ዘግቧል፡፡ የኬንያ፣ የጅቡቲና የሶማሊያ ፕሬዚዳንቶችም ድርጊቱን አውግዘው ከኢትዮጵያ ህዝብና መንግሥት ጎን እንቆማለን ማለታቸውን የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖረሽን ዘግቧል።