የሃገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ተወያየ

Your browser doesn’t support HTML5

የሃገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ተወያየ

በሀገራዊ ምክክር ወቅት ሕዝቡ የሚሰጠውን ማንኛውንም ውሳኔ እንደሚቀበሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ መግለፃቸውን የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ገለፀ።

የኮሚሽኑ አባላት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር ትናንት ለመጀመሪያ ጊዜ መወያየታቸውን የኮሚሽኑ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ለቪኦኤ ገልፀዋል።

በምርጫ ቦርድ እውቅና ካላቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል አርባዎቹ ከኮሚሽኑ ጋር ለመሥራት መስማማታቸውንና ከተቀሩት አሥራ ሦስት ፓርቲዎች ጋር በሚያነሷቸው ቅሬታዎች ዙሪያ እየተወያዩ መሆናቸውን ፕሮፌሰር መስፍን ተናግረዋል።

በመላ ሃገሪቱ ሰላም ሳይሰፍን አካታች ውይይት እንዴት ማካሔድ ይቻላል? ለሚል ጥያቄም ሰብሳቢው መልስ ሰጥተዋል።