የሚነሱ ቅሬታዎች ሚዛናዊነትን፥ የጋራ እሴቶቻችንንና መርኆችን በጠበቀ መንገድ መቅረብ አለባቸው ሲሉ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ መክረዋል።
ሀዋሳ —
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ በሆሳዕና ከተማ ከሃዲያ ህዝብ ተጠሪዎች ጋር ተሰብስበው መክረዋል።
ተሰብሳቢዎቹ አሉብን ያሏቸውን ጥያቄዎች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ያቀረቡ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩም በክልሉ በአንድነት ለመቆየት ያነሱትን ሃሳብ አድንቀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ በሐዲያ ዞን ያደረጉትን ጉብኝት፣ ከሕዝብ ተጠሪዎች ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ የተነሡ አስተያየቶችንና የተሰጡ መልሶችን ያካተተውን ዘገባ ከተያይዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5