ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለትጥቅ ትግል ተፋላሚዎች የሰላም ጥሪ አቀረቡ

Your browser doesn’t support HTML5

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለትጥቅ ትግል ተፋላሚዎች የሰላም ጥሪ አቀረቡ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሰላም ጥሪውን ያቀረቡት፣ በባሕር ዳር ከተማ ከአራት ዓመት በፊት ግንባታው የተጀመረውና ከ1ነጥብ4 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ እንደተጠናቀቀ በተገለጸው የዓባይ ድልድይ የምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ ነው።

"አላስፈላጊና ኢትዮጵያን የማያሻግር ጉዞ ነው፤" ያሉት “መገዳደልና ጥፋት ይብቃን” ሲሉም ተደምጠዋል። "ወንድሞች" ሲሉ የጠሯቸውንና "በጫካ የሚገኙ አካላትን" ከክልሉ መንግሥት ጋራ አብረው እንዲሠሩ ጥሪ አቅርበዋል።

በጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ላይ አስተያየታቸውን እንዲሰጡን የጠየቅናቸው የእናት ፓርቲ ፕሬዚዳንት እና አምስት የፖለቲካ ፓርቲዎችን በውስጡ ያቀፈው የ"ትብብር ፓርቲዎች" የወቅቱ ሊቀ መንበር ዶር. ሰይፈ ሥላሴ አያሌው፣ የጠቅላይ ሚንስትሩ ንግግር "መፍትሔ ሊያመጣ የሚችል የሰላም ጥሪ አይደለም፤" ብለዋል።