የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የወረባቦ ቆይታ

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በወረባቦ /ጥቅምት 15/2020 - ምንጭ፤ የጠ/ሚ ፅ/ቤት ሳይት/

የበረሃ አንበጣ ወረርሽኝ የዘንድሮ የኢትዮጵያ የሰብል ምርት እስከ አምስት ከመቶ እንዲቀንስ እንደሚያደርግ ተገልጿል።

ዛሬ ደቡብ ወሎ ውስጥ ተገኝተው ወርባቦ ወረዳን ያዩትና ከአርሶ አደሮች ጋር የተነጋገሩት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጉዳት ለደረሰባቸው መንግሥት ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።

የአንበጣውን ወረርሽኝ በ79 ከመቶ መቆጣጠር መቻሉንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

ወረርሽኙ በምሥራቃዊ አማራና በአፋር ክልል 700 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ጉዳት ማድረሱ ተገልጿል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚያው ቆይታቸው ወቅት ከሁለት ቢሊዮን ብር በላይ በጀት የተመደበለትን የሃይቅ - ቢስቲማ ጭፍራ መንገድ ማስጀመራቸው ታውቋል።

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሀመድ በወረባቦ