ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ ያሸነፉት የዘንድሮ የኖቤል የሰላም ሽልማት ለኢትዮጵያ ሕዝብ የተበረከተ የአደራ ሽልማት ነው ሲል ጽህፈት ቤታቸው አስታወቀ።
አዲስ አበባ —
በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የፕሬስ ሐላፊ ንጉሱ ጥላሁን በሰጡት መግለጫ፤ "ሽልማቱ የሚያዘናጋ ሳይሆን ለበለጠ ሥራ የሚነሳሳ እና ኢትዮጲያውያን አንድ ከሆንን ምን ማከናወን እንደምንችል ያመላከተ ነው" ብለዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትሩን ስሜት ያጋሩ የቅርብ ሰዎችም እንደዕዳ ይቆጠራል ማለታቸውን ገልጸዋል።
የኖቤል የሰላም ሽልማቱ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ እና ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ መድረኮች ያላቸውን ተሰሚነት የሚጨምር መሆኑን ደግሞ የአሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው አስተያየት ሰጪዎች ተናግረዋል
(እስክንድር ፍሬው ያጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)
Your browser doesn’t support HTML5