አዲስ ተጨማሪ የሽያጭ ግብር በማሕበረሰቡ ላይ ምን አይነት ጫና ያሳደር ይሆን?

አቶ ያሬድ ኃይለመስቀል/የምጣኔ ሃብት ባለሙያ

Your browser doesn’t support HTML5

አዲስ ተጨማሪ የሽያጭ ግብር በማሕበረሰቡ ላይ ምን አይነት ጫና ያሳደር ይሆን?

የገንዘብ ሚንስቴር ባለፉት 22 ዓመታት ከተጨማሪ እሴት የሽያጭ ግብር ነፃ ተደርገው ቆይተዋል ባላቸው የኤሌክትሪክ ፣ የውሃ አቅርቦት እና የትራንስፖርት ዘርፍ ላይ ተጨማሪ እሴት ግብር ተግባራዊ ማድረግ እንደሚጀምር ነሐሴ 23, 2016ዓ.ም በማሕበራዊ የትስስር ገጹ ባወጣው የጽሁፍ መግለጫ አስታውቋል፡፡

ይህ ተጨማሪ እሴት ታክስ ቋሚና አነስተኛ ገቢ ያለው ማህበረሰብ ላይ ጫና የሚፈጥር ነው ሲሉ የአሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው የምጣኔ

ሃብት ባለሙያ እና የኢንቨስትመንት አማካሪው አቶ ያሬድ ኃይለመስቀል ይናገራሉ፡፡