ማይክ ፔንስ ደቡብ ኮሪያ ናቸው

  • ቪኦኤ ዜና

የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዚዳንት ማይክ ፔንስ

ሰሜን ኮሪያ የኒውክሊየር እና የተወንጫፊ መሣሪያ መርኃ ግብሮቿን እንድታቆም ዩናይትድ ስቴትስ ከአጋሮችዋ ጋር ሆና ከባድ ግፊት እንደምታደርግ የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዚዳንት ማይክ ፔንስ ለደቡብ ኮሪያ አረጋገጡ፡፡

ሰሜን ኮሪያ የኒውክሊየር እና የተወንጫፊ መሣሪያ መርኃ ግብሮቿን እንድታቆም ዩናይትድ ስቴትስ ከአጋሮችዋ ጋር ሆና ከባድ ግፊት እንደምታደርግ የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዚዳንት ማይክ ፔንስ ለደቡብ ኮሪያ አረጋገጡ፡፡

ምክትል ፕሬዚዳንት ፔንስ ዛሬ ደቡብ ኮሪያ ገብተዋል።

ፒዮንግያንግ በደቡብ ኮሪያ በሚካሄደው ኦሎምፒክ ውድድሮች አጋጣሚውን ተጥቅማ ለማማለል የምታደርገውን ሙከራ ለመቀናቀን አቅደዋል። አካሄዳቸው በፒዮንግያንግ ላይ ተፅኖ ለመፍጠር በሚካሄደው እንቅስቃሴ ደቡብ ኮሪያ በያዘችው ጥረት ዙሪያ መቃቃር ሊፈጥር ይችላል፡፡

ምክትል ፕሬዚዳንቱ ቀደም ብለው ጃፓን ውስጥ ሲናገሩ ከሰሜን ኮሪያ ጋር ያለው የኒውክሊየር ፍጥጫ በሰላማዊ መንገድ መፍትኄ እንዲያገኝ ዩናይትድ ስቴትስ ትፈልጋለች፤ ካስፈለገም ኃይል ለመጠቀም ዝግጁ ነች ብለዋል።