የፈረንሳይ ፕሬዚደንት ኢማኑኤል ማክሮን የንግድ መሪዎችና ሃምሳ የዓለም መሪዎችን ያሰባሰበ፣ የአየር ንብረት ለውጥን ለመዋጋት የሚያስፈልገውን ወጭ ማጠናከር ላይ ያተኮረ ጉባዔ ዛሬ ፓሪስ ውስጥ ከፍተዋል።
ዋሺንግተን ዲሲ —
የፈረንሳይ ፕሬዚደንት ኢማኑኤል ማክሮን የንግድ መሪዎችና ሃምሳ የዓለም መሪዎችን ያሰባሰበ፣ የአየር ንብረት ለውጥን ለመዋጋት የሚያስፈልገውን ወጭ ማጠናከር ላይ ያተኮረ ጉባዔ ዛሬ ፓሪስ ውስጥ ከፍተዋል።
የዛሬ የመሪዎች ጉባዔ የተከፈተው ወደሁለት መቶ የሚጠጉ ሃገሮች የፓሪሱን የአየር ንብረት ስምምነት ከፈረሙ ሁለት ዓመታት በኋላ መሆኑ ነው።
ውሉ ሀገሮች የበካይ ጋዝ ልቀታቸውን መጠን እንዲገድቡ እና ባለጸጎቹ ሃገሮች ታዳጊዎቹን ሃገሮች በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የሚደርስባቸውን ጉዳት ለመቋቋም እንዲረዷቸው ይጠይቃል።
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ በፓሪሱ ጉባዔ ላይ እንዲካፈሉ አልተጋበዙም። ፕሬዚደንቱ የፓሪሱ ውል ሌሎች ሀገሮች የሚጠቀሙበት እና ዩናይትድ ስቴትስን የሚጎዳ ነው በማለት ሃገራቸውን ከውሉ ማስወጣታቸው ይታወሳል።