Your browser doesn’t support HTML5
የዩናይትድ ስቴትስ የኢሚግሬሽን-ነክ ጉዳዮችና አዲሱ ፕሬዝዳንታዊ ማዘዣ
Your browser doesn’t support HTML5
የውይይቱን ሁለተኛ ክፍል ከዚህ ያድምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5
የውይይቱን ሦሥተኛና የመጨረሻ ክፍል ከዚህ ያድምጡ።
በብዙ ሚልዮን የሚቆጠሩ በዩናይትድ ስቴትስ የሚኖሩ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸውንና ሌሎችን ያሳሰበ ርዕሰ ጉዳይ ነው።
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ባሳለፍነው ሳምንት መገባደጂያ ያወጡትን አዲሱን ፕሬዝዳንታዊ ማዘዣ ጨምሮ በዩናይትድ ስቴትስ የኢሚግሬሽን ፖሊሲ ዙሪያ እየመጡ ያሉና “ይመጡ ይሆናል” የተባሉ ለውጦችና አንድምታ በጥልቀትና በቅርበት ለማየት የሚጥር ከሕግ ባለሞያዎች ጋር የተካሄደ ውይይት ነው።
ተወያዮች:- የሚ ጌታቸው በካሊፎኒያ ክፍለ ግዛት በሳንሆዜ የአሜሪካ የሕግ-ጠበቆች ማኅበር የሳንታክላራ ቫሊ ሊቀመንበር ናቸው። በስደተኞች ጉዳይ ተሟጋችነትም ይታወቃሉ።
አቶ ፍጹም አቻምየለህ በዋሽንግተን ዲሲና ቨርጂኒያ በጥብቅና ሥራ የተሰማሩና በስደተኞች ሕግ ዙሪያ ለረዥም ጊዜ ያገለገሉ ናቸው።
አቶ ተክለሚካኤል አበበ ደግሞ በካናዳ ቶሮንቶ በጥብቅና ሥራ የተሰማሩ ናቸው። የውይይቱን የመጀመሪያ ክፍል ከዚህ ያድምጡ።