የፓኪስታን ፀረ-ሙስና ፍርድ ቤት፣ በአንድ የአገሪቱ ተቃዋሚ መሪ ላይ ክስ መሰረተ።
ዋሺንግተን ዲሲ —
በተቃዋሚ መሪው ሻሀባዝ ሻሪፍ ላይ በዛሬው ዕለት የተመሰረተው ክስ፣ ላሆር ውስጥ ከሚገነባ የመኖሪያ ቤቶች ህንፃ ሥራ ጋር በተያያዘ ሲሆን፣ የቤቶቹን የሥራ ኮንትራት እርሳቸው አባል ለሆኑበት ለፓኪስታኑ የሙስሊም ሊግ ፓርቲ ሰዎች ሰጥተዋል ተብለው ነው።
ከዚህ የሙስና ቅሌት ጋር በተያያዘ፣ ሌሎች 7 ሰዎችም ተከሰዋል። ይሁንና፣ ተጠርጣሪው የተቃዋሚ መሪ ሸሪፍ፣ «መሰረተ-ቢስ የሆነ የሀሰት ውንጀላ» በማለት፣ በአንድ የፓኪስታን ጋዜጣ ላይ በሰጡት ቃል አስተባብለዋል።
የተጠርጣሪው ወንድምና የቀድሞው የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ናዋዝ ሻሪፍ እአአ በ2017 በሙስና ቅሌት ከሥልጣን መነሳታቸውን ልብ ይሏል!