የቀድሞ የፓኪስታን ጠ/ሚ ናዋዝ ሻሪፍ ልጃቸው ማሪያምና አማቻቸው መሃመድ ሳፍዳር የተመሰረቱባቸው የሙስና ክሶች ተቋርጠው እንዲለቀቁ የሀገሪቱ ከፍተኛ ፍ/ቤት አዘዘ።
ዋሺንግተን ዲሲ —
የቀድሞ የፓኪስታን ጠ/ሚ ናዋዝ ሻሪፍ ልጃቸው ማሪያምና አማቻቸው መሃመድ ሳፍዳር የተመሰረቱባቸው የሙስና ክሶች ተቋርጠው እንዲለቀቁ የሀገሪቱ ከፍተኛ ፍ/ቤት አዘዘ።
ሻሪፍ እና የቤተሰባቸው አባላት ያቀርቡት ይግባኝ ውሳኔ እስኪያገኝ እንዲለቀቁ የሰጠውን ውሳኔ ተከትሎ ዛሬ ማምሻውን መለቀቃቸውን ለማወቅ ተችሏል።
ባለፈው ሐምሌ ወር ነበር ሦስቱን ተከሳሾች የፀረ ሙስና ልዩ ችሎት በውጭ ሀገሮች ከሚታውቁ የገቢ ምንጫቸው በላይ ንብረቶች እንዳሏቸው ደርሰንበታል ብሎ የቀድሞውን ጠ/ሚ በአስር ዓመት ልጃቸው በሰባት ዓመት አማችየው በአንድ ዓመት እስራት እንዲቀጡ የፈረደባቸው።