Your browser doesn’t support HTML5
በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በተከሠቱና በቀጠሉ ግጭቶች፣ የተፈጥሮ አደጋዎች እና ተያያዥ ችግሮች ምክንያት፣ ከአምስት ሺሕ በላይ ትምህርት ቤቶች ከአገልግሎት ውጪ መኾናቸውን ያስታወቀው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን፣ በዚኽም ምክንያት ከአምስት ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ መኾናቸውን ገልጿል።
የትምህርት ተቋማት ውድመት እና ከአገልግሎት ውጪ መኾን፣ በሕፃናት የወደፊት ተስፋ እና በሀገር ላይ እያደረሰ ያለውን ጉዳት አስመልክቶ፣ ስመኝሽ የቆየ ተማሪዎችንና ባለሞያዎችን አነጋግራ ተከታዩን ዘገባ አዘጋጅታለች።