ኦሮሞ ተማሪዎች ተፈቱ

  • ቪኦኤ ዜና

ከኦሮሚያ የተማሪዎች ተቃውሞ ሰልፎች አንዱ /ፎቶ ፋይል -ግንቦት 2013 ዓ.ም/

Your browser doesn’t support HTML5

ኦሮሞ ተማሪዎች ተፈቱ

ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር ተያይዞ በኦሮሚያ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ተቀስቅሶ ከነበረው ተቃውሞና ከተከተለውም ሁከት ጋር ተያይዞ በቁጥጥር ሥር ውለው የነበሩ ስድስት ኦሮሞ ተማሪዎች መለቀቃቸውን የቪኦኤ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡

የተለቀቁት ተማሪዎች አዱኛ ኬሶ፣ ቢሊሱማ ዳመና፣ ሌንጂሳ ዓለማየሁ፣ አብዲ ከማል፣ መገርሳ ወርቁና ቶፊቅ ራሺድ የሚባሉ ሲሆኑ ክሥ ሳይመሠረትባቸው ለአንድ ዓመት ከሦስት ወር መታሠራቸው ታውቋል፡፡

ከሁለት ወራት በፊትም ኒሞና ጫሊ የሚባል ተማሪ እንዲሁ ክሥ ሳይመሠረትበት የተለቀቀ ሲሆን አስላን ሃሰን የሚባል ተማሪ ግን በፖሊስ ቁጥጥር ሥር እንዳለ መሞቱ ተገልጧል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡