Your browser doesn’t support HTML5
የቀበሌ አስተዳደር መዋቅሮችን መልሶ ማዋቀሩን ያስታወቀው የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት፣ የመዋቅሩ አላማም የአገልግሎት አሰጣጡን ማሻሻል መሆኑን አመልክቷል።
የክልሉ የሕበረተሰብ አገልግሎት እና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ኮከበ ዲዳ ለአሜሪካ ድምፅ ሲናገሩ፣ አዲሱ አወቃቀር ለቀበሌዎች ከቀድሞው የተሻለ ኃላፊነት እንደሚሰጥ ገልጸዋል። በክልሉ የሚገኙ ከሰባት ሽህ በላይ ቀበሌዎች በአዲስ መልክ መዋቀራቸው፣ በአብዛኛው በወረዳዎች ይሰጡ የነበሩ አገልግሎቶችን ለመስጠት እንደሚያስችላቸውም ጠቅሰዋል።
የተቃዋሚው፣የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ምክትል ሊቀ መንበር አቶ ሙላቱ ገመቹ ግን መንግስት የቀበሌ መዋቅሮችን፣ የቁጥጥርና የጭቆና ዘዴ አድርጎ ሊጠቀም እንደሚችል በመግለፅ እርምጃውን ተችተዋል።