የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ቃል አቀባይ ስለ አዲሱ ካቢኔ ይናገራሉ

  • እስክንድር ፍሬው

የኦሮሚያ ክልል ካርታ

"ሰሞኑን ይፋ የተደረገው አዲስ ካቢኔ የህዝቡን ፍላጎት ሊያረካ የሚችል፣ የመልካም አስተዳደር ጥያቄን የሚመልስና የመንግሥትን የማስፈፀም አቅም የሚያሳድግ ነው” ሲል የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት አስታወቀ፡፡

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የሚመለከተው የፀጥታውን ሁኔታ መሆኑን የጠቆሙት የክልሉ መንግሥት ቃል አቀባይ አቶ ፈቃዱ ተሰማ “የተቀሩት ሥራዎች ግን በተለመደው መንገድ ይቀጥላሉ” ብለዋል፡፡

በዚሁም መሠረት የህዝቡን ፍላጎት ለማርካትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄን ለመመለስ በትጋት እንደሚሠራ የክልሉ ቃል አቀባይ ተናግረዋል፡፡

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የኮሙዩኒኬን ጉዳዮች ኃላፊ የሆኑትን አቶ ፈቃዱ ተሰማን ያነጋገራቸው እስክንድር ፍሬው ተከታዩን ዘገባ ልኳል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ቃል አቀባይ ስለ አዲሱ ካቢኔ ይናገራሉ