ወባ ከግጭት በበለጠ ሰውን እየገደለ መኾኑን የምሥራቅ ወለጋ ዞን ነዋሪዎች ተናገሩ

የወባ ትንኝ

በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ዞኖች የተከሠተው የወባ ወረርሽኝ፣ “የሰው ሕይወትን እየቀጠፈ ነው፤” ያሉ ነዋሪዎች፣ በተለይም በምሥራቅ ወለጋ ዞን ክፉኛ መዛመቱንና ለዓመታት የቀጠለው ግጭት ከሚያደርሰው ጉዳት በበለጠ ሰዎችን እየገደለ መኾኑን አመልክተዋል።

Your browser doesn’t support HTML5

ወባ ከግጭት በበለጠ ሰውን እየገደለ መኾኑን የምሥራቅ ወለጋ ዞን ነዋሪዎች ተናገሩ

የአሜሪካ ድምፅ በስልክ ያነጋገራቸው በዞኑ የሚገኙ አንድ የሕክምና ዶክተርም፣ ከታካሚዎቻቸው መካከል 90 በመቶዎቹ ከባድ የወባ ምልክት ያለባቸው ታማሚዎች መኾናቸውን ጠቁመዋል።

በተለያዩ ዞኖች ያለው የጸጥታ ችግር እና አለመረጋጋት፣ የወባ ትንኝን በመከላከል እንቅስቃሴው ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ማሳደሩንም ነዋሪዎቹ አክለው ገልጸዋል።

የኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ ዶር. ተስፋዬ ክበበው ለአሜሪካ ድምፅ ሲናገሩ፣ የወባ በሽታ ስርጭት፣ ባለፉት ሳምንታት በዕጥፍ መጨመሩን ገልጸው፣ ችግሩን የሚመጥን ርምጃ መውሰድ እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል።