በአርሲ ዞን አኖሌ አካባቢ የተሰራዉ ሃዉልት ቂም ቀስቃሽ ነዉ ተበለ፥ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በበኩሉ የተፈጸሙ ድርጊቶች እንዳይደገሙ ለማስታወስ ነዉ ሲል አስተባበለ።

  • እስክንድር ፍሬው

Your browser doesn’t support HTML5

በአርሲ ዞን አኖሌ አካባቢ የተሰራዉ ሃዉልት


በአርሲ ዞን ሂጦሳ ወረዳ እየተገነባዉና በቅርቡ የሚመቀ የአኖሌ ሃዉልት አብሮት የተገነባዉን ቤተመዘክር ጨምሮ ሃያ ሚሊዮን ብር የወጣበት መሆኑን የኦሮሚያ ክልል መረጃ ያመለክታል።

የተቆረጠ ጡት በተቆረ ጡት በተቆረጠ እጅ ላይ የሚያሳየዉ ሃዉልት ከተቃዋሚዉ የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት አሉታዊ አስተያዬት ቀርቦበታል።

የመኢአድ ፕሬዚደንት አቶ አበባዉ መሃሪ "አጼ ሚኒሊክ ኢትዮጵያን አንድ ለማድረግ ታላቅ ስራ የሰሩ መሪ መሆናቸዉን ወደ ጎን ትተዉ መጥፎ ስም በመስጠት ያልተደረገዉን ተደረገ በማለትመኮንኑ ተገቢ አይመስለኝም። የኦሮሞ ሕዝብ ታላቅ ታሪክ ያለዉ ሕዝብ ነዉ፥ አጼ ሚኒልክ በኦሮሞ ላይ ይህን አድገዋል፤" ብሎ መናገር ሕዝቡን ማሳነስ ነዉ ሲሉ አስተያየታቸዉን አክለዋል። "ታሪኩ አልተፈጸመምና የኦሮሞ ተወላጆች የሃዉልቱ መቆም ስህተት መሆኑን አሳስባለሁ ብለዋል።"አቶ አበባው።

የኦሮሚያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ አቶ መሃመድ ጂሎ በሰጡት ምላሽ የሃዉልቱ ዓላማ እንደተባለዉ ቂም በቀል መቀስቀስ ሳይሆን ይልቁንስ የተፈጸመዉ ድርጊት እንዳይደገም ለማስታወስ ነዉ ብለዋል። ”የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስትም ሆነ ኦሮሞ ሕዝብ አንድ ብሔር ነዉ ይህን ችግር ያደረሰብኝ የሚል ግንዛቤ የለዉም” ጥሉም ትግሉም ከስርዓቱ ጋር ነዉ የነበረዉ ብለዋል። የመኢአድ ተቃዉሞ የጠበቅ ነዉ ነዉ ያሉት አቶ መሃመድ ጂሎ ሕዝቡ በፌዴራላዊ ክልል ተደራጅቶ ቋንቋዉን መጠቀሙን ጭምር መአኢድ ይቃወማል ሲሉ ከሰዋል።