በኦሮምያና በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል አዋሳኝ ወረዳዎች ግጭት ዙሪያ ጠ/ሚ ኃይለማሪያም አስተያየት ሰጡ

  • እስክንድር ፍሬው

አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ

በኦሮምያና በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ ወረዳዎች በታጣቂዎች ይፈፀማል የተባለውን ጥቃት ለማስቆም የሁለቱ ክልሎች መንግሥታት በጋራ እየሠሩ መሆናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ አስታውቀዋል።

በኦሮምያና በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ ወረዳዎች በታጣቂዎች ይፈፀማል የተባለውን ጥቃት ለማስቆም የሁለቱ ክልሎች መንግሥታት በጋራ እየሠሩ መሆናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ አስታውቀዋል።

“ፌደራል መንግሥቱም የቅርብ ድጋፍ እያደረገ ነው” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

በግጭቶቹና በጥቃቶቹ ውስጥ እጆቻቸውን አስገብተዋል የተባሉ የአመራር አባላት መኖራቸውንም አቶ ኃይለማርያም ተናግረዋል።

በኦሮምያና በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል አዋሳኝ ወረዳዎች የሚፈፀመውን ጥቃት በተመለከተ ጠ/ሚ ኃይለማሪያም አስተያየት ሲሰጡ የመጀመሪያው ነው፡፡

ሰሞኑን እየተከበረ ያለውን ዓለምቀፍ የሴቶች ቀን አስመልክቶ ከተለያዩ የሀገሪቷ አካባቢዎች ከመጡ 2 ሺሕ 5 መቶ ሴቶች ጋር በፅ/ቤታቸው የተወያዩት ጠ/ሚኒስትሩ ከቀረቡላቸው ጥያቄዎች አንዱ ይሄንኑ የታጣቂዎች ጥቃት መነሻ ያደረገ ነበር፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

በኦሮምያና በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል አዋሳኝ ወረዳዎች ግጭት ዙሪያ ጠ/ሚ ኃይለማሪያም አስተያየት ሰጡ