በተለያየ ደረጃ በሚገኙ በሺህዎቹ የሚቆጠሩ የአመራር አባላት ላይ ዕርምጃ መውሰዱን የኦሮምያ ገዢ ፓርቲ /ኦህዴድ/ አስታወቀ፡፡
አዲስ አበባ —
በተለያየ ደረጃ በሚገኙ በሺህዎቹ የሚቆጠሩ የአመራር አባላት ላይ ዕርምጃ መውሰዱን የኦሮምያ ገዢ ፓርቲ /ኦህዴድ/ አስታወቀ፡፡ ያልተገባ አሰራር ሲከተሉ ነበር ያላቸውን ከ2ሺህ በላይ አመራሮች ከኃላፊነት ማንሳቱን 5መቶ አርባ የሚሆኑትን ከደረጃ ዝቅ ማድረጉን ከ3ሺ በላይ የሚሆኑትን ደግሞ ከአባልነት መሰሩዙን ነው ያስታወቀው፡፡
ለሦስት ቀናት የተካሄደው የኦህዴድ ስምንተኛው ድርጅታዊ ጉባዔ ሊቀመንበሩና የሀገሪቱ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ በተገኙበት ዛሬ ከሰዓት ተጠናቋል፡፡
በዚሁ ጉባዔ ዙሪያ የኦህዴድ የፖለቲካ እና አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ የሆኑትን አቶ ከፍያለው አያናንን አነጋግረናል፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5