ኦሮሚያ በከፊል ግር፣ በከፊል ጭር፡- የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ማግሥት

  • ሔኖክ ሰማእግዜር

ከእስር ለተፈቱ የተደረገ አቀባበል

የኢትዮጵያ መንግሥት ከአርብ ጀምሮ ይፋ ያደረገውን የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ተከትሎ በአንዳንድ የኦሮሚያ ከተሞች ከእስር ለተፈቱ በአደባባይ ህዝብ ወቶ አቀባበል ሲያደርግ፤ ሌሎች ከተሞች ጭር ብለው ታይተዋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ከአርብ ጀምሮ ይፋ ያደረገውን የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ተከትሎ በአንዳንድ የኦሮሚያ ከተሞች ከእስር ለተፈቱ በአደባባይ ህዝብ ወቶ አቀባበል ሲያደርግ፤ ሌሎች ከተሞች ጭር ብለው ታይተዋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁን ዝርዝር በትናንትናው ዕለት ያስረዳ ሲሆን፤ በተለይ በቡድን መደራጀትና በአደባባይ ሰልፍ ማድረግ የከለከለ ቢሆንም፤ በኦሮሚያ አንዳንድ አካባቢዎች፤ ከእስር ለተፈቱ አቀባበል እንደተደረገ ተቃዋሚው የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ገልጿል።

በምእራብ ወለጋ በቅርቡ ከእስር ለተፈቱ የተደረገው አቀባበል፤ በሰላም መጠናቀቁን ነው ኦፌኮ ያስታወቀው።

ከዚህ ቀደም በየአካባቢው ጦር መስፈሩን የተናገሩት አቶ ሙላቱ ገመቹ፤ የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁን ተከትሎ ከዚህ ቀደም የተለየ የወታደር እንቅስቃሴ እንዳልታየ ተናግረዋል።

በሰሜን ሸዋ ገርበ ጉራሻ ከተማ ለደኅንነቱ በመስጋት ስሙን ያልጠቀሰ የከተማዋ ነዋሪ፤ የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁን ተከትሎ፤ ከተማዋ ፀጥ ብላ መቆየቷንና ወጣቶችም ተሰባስበው እንደማይንቀሳቀሱ ተናግሯል።

ለተጨማሪ የተያያዙትን የድምፅና የቪድዮ ዘገባዎች ያዳምጡ፣ ይመልከቱ።

Your browser doesn’t support HTML5

ኦሮሚያ በከፊል ግር፣ በከፊል ጭር፡- የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ማግሥት