በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ዞኖች ውስጥ ሰሞንኑ የተደረጉ ሰልፎች ከተለያዩ ክልሎችና የኦሮሚያ ከተሞች ሆን ብለው በተደራጁ ሰዎች የተመሩ መሆናቸውን መረጃ እንደደረሰው የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት አስታወቀ።
ዋሽንግተን ዲሲ —
በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ዞኖች ውስጥ ሰሞንኑ የተደረጉ ሰልፎች ከተለያዩ ክልሎችና የኦሮሚያ ከተሞች ሆን ብለው በተደራጁ ሰዎች የተመሩ መሆናቸውን መረጃ እንደደረሰው የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት አስታወቀ።
በድርጊቱ የተሳተፉ ናቸው የተባሉ ከ100 በላይ ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው ነውም ብሏል። በዚህ እንቅስቃሴ ውስጥ የሰው ሕይወት ጠፍቷል ንብረት ወድሟል። ለጠፋው ንብረት ግጭቱን ያነሳሱትን ሰዎች ተጠያቂ ያደረገው የክልሉ መንግሥት የሰው ሕይወት የጠፋውም ግጭቱን ለማብረድ በፀጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት ነው ብሏል።
በሌላ በኩል ከዚህ ቀደም የተቃውሞ እንቅስቃሴዎችን በድረ ገጽ በመምራት የሚታወቀው የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ ሥራአስኪያጅ አቶ ጃዋር መሐመድ፤ የሰሞኑ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ከዚህ ቀደም የነበረውን ተቃውሞ ይመሩት የነበሩት ወጣቶች እንዳልጠሩት አስቀድመን መረጃ ስንሰጥ ነበር ብሏል።
በተያያዘ ከወራት በፊት በሕገወጥ መንገድ ሲጓጓዝ ቦርደዴ ላይ በቁጥጥር ስር ውሎ እንደነበር የተገለፀው ከ541 ሺሕ ዶላር በላይ ከሶማሌ ክልል ለተፈናቀሉ ነዋሪዎች እንዲሰጥ ፍርድ ቤት ወስኗል።
የጽዮን ግርማን ዝርዝር ዘገባ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።