በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ዞኖች ታጣቂዎች የተወገዙበት የሰላም ጥሪ የተላለፈበት ሰልፍ መካሄዱ ተገለጸ

የኦሮምያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ኮሚኒኬሽን ኃላፊ አቶ ሀይሉ አዱኛ

Your browser doesn’t support HTML5

በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ዞኖች ታጣቂዎች የተወገዙበት የሰላም ጥሪ የተላለፈበት ሰልፍ መካሄዱ ተገለጸ

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ፣ ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብና ቄለም ወለጋ፣አርሲ፣ጉጂ ዞኖችና የተለያዩ ወረዳዎች የሰላም ጥሪ ታጣቂዎች የተወገዙበትና የሰላም ጥሪ የተላለፋባቸው ሰልፎች መካሄዳቸውን ተሳታፊዎች ለአሜሪካ ድምጽ ገለጹ። አንዳንዶች ሰልፉ በመንግሥት አስተባባሪነት እንደተዘጋጀ ሲናገሩ፣ ሌሎች ደግሞ "መንግሥትና ታጣቂው ቡድን ሰላም እንዲያወርዱ ለመጠየቅ በኅብረተሰቡ የተዘጋጀ ነው" ብለዋል።

የኦሮሚያ ክልል ኮምዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ፣ አቶ ኃይሉ አዱኛ "መንግሥት ሰልፉን በማስተባበር ውስጥ እጁ የለበትም" ብለዋል። ከኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎች ተወካይ በኩል ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡