በኦሮምያ ባሌ ዞን ሦስት ወረዳዎችና ሶማሌ ክልል ውስጥ ደግሞ ሊበን ወረዳ ውስጥ በተነሳ የኮሌራ ወረርሽኝ ሃያ ሰው መሞቱን የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዓዊ አገልግሎቶች ማስተባበሪያ ቢሮ አስታውቋል።
ባለፉት ጥቂት ወራት ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ሰው ለወረርሽኙ መጋለጡን ቢሮው ትናንት ባወጣው መግለጫ አመልክቷል።
በሌላ በኩል ግን የሞተው ሰባት ሰው እንደሆነና በርበሬ ወረዳ ውስጥ ለታመሙት ህክምና እየተሰጠ መሆኑን የባሌ ዞን ጤና ፅህፈት ገልጿል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በምሥራቅ ባሌ ዞን ግንኢር ወረዳና ግንኢር ከተማ፣ እንዲሁም ምዕራብ ወለጋ ውስጥ ኩፍኝ መቀስቀሱም ታውቋል።
ምዕራብ ወለጋ ያለው የፀጥታ ችግር በአካባቢዎቹ ተከስቷል የተባለው የኩፍኝ ወረርሽኝ እንዲባባስ ምክንያት መሆኑና ክትባት ለማድረስና ለመስጠትም አስቸጋሪ ሁኔታ መፍጠሩን ነዋሪዎችና ባለሥልጣናት ለቪኦኤ ተናግረዋል።
/ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ይከታተሉ/
Your browser doesn’t support HTML5