በምዕራብ ኦሮምያ ማዘዣ ማዕከል ታስረው የነበሩ የነቀምቴ ወንጀል መከላከል ኃላፊና የነቀምቴ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሃኪም ተለቀቁ፡፡
ነቀምት —
በኩምሳ ሞረዳ ቤተ መንግሥት ውስጥ ታስረው የሚገኙ ትናንት የረሃብ አድማ መምታታቸውን አንዳንድ የታሳሪ ቤተሰቦች ተናገሩ፡፡ በጊምቢም “የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ታጣቂዎችን ትደግፋላችሁ” በሚል ምክንያት ከ100 በላይ ሰዎች ታስረዋል ሲሉ አንድ የታሳሪ ቤተሰብ ገልፀዋል፡፡
የኦሮሚያ ፀጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ኮሎኔል አበበ ገረሱ በጦርነት ላይ እያሉ የተማረኩትን ወደ ህግ ማቅረብ ብሎ ነገር የለም፣ ሰው በመግደልና ቦምብ በመወርወር የተጠረጠሩ ሰዎች ደግሞ በህግ ይጠየቃሉ ብለዋል፡፡
የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5