ተቃዋሚ ፓርቲዎችና ገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግ ቀደም በለው በሰየሙትና በተወካዮች ምክር ቤት ባለሞያዎች አማካኝነት በቀረበላቸው የክርክር እና የድርድር የአሰራር ረቂቅ ደንብ ላይ ለመወያየት ሌላ ቀጠሮ ተለዋወጡ፡፡
አዲስ አበባ —
ተቃዋሚ ፓርቲዎችና ገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግ ቀደም በለው በሰየሙትና በተወካዮች ምክር ቤት ባለሞያዎች አማካኝነት በቀረበላቸው የክርክር እና የድርድር የአሰራር ረቂቅ ደንብ ላይ ለመወያየት ሌላ ቀጠሮ ተለዋወጡ፡፡ መገናኛ ብዙሃን ያለ ልዩነት በውይይቱ ገብተው እንዲዘግቡ ፓርቲዎቹ ተስማሙ፡፡
በስፍራው ለነበሩ ጋዜጠኞች አዳራሹ ክፍት ሲደረግ ከመድረኩ መሪ እንደተነገረው ከሆነ የዕለቱ አጀንዳ አንድ ብቻ ነበር፡፡
አጀንዳው የፖለቲካ ፓርቲዎች ክርክርና ድርድር የአሰራር ረቂቅ ደንብ ላይ መነጋገር የሚል እንደሆነም በፓርቲዎቹ ስምምነት መድረኩን ይመሩት የነበሩትና የኢሕአዴግ ፅ/ቤት ምክር ቤት ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ለጉባዔው አስታውሰዋል፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
Your browser doesn’t support HTML5