የጠቅላይ ሚኒስትሩ እና የፖለቲካ ፓርቲዎች ውይይት

Your browser doesn’t support HTML5

የጠቅላይ ሚኒስትሩ እና የፖለቲካ ፓርቲዎች ውይይት

ከስድስት ዓመት በፊት በዛሬው ቀን የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ነው ቃለ መሐላ የፈጸሙት ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)፣ 400 ከሚኾኑ አገር አቀፍ እና ክልላዊ ፓርቲዎች አመራሮች ጋራ ትላንት በዋዜማው ሲወያዩ፣ የ13 ፖለቲካ ፓርቲዎች ጥምረት በውይይቱ ላይ አለመሳተፉ ታውቋል፡፡

ከውይይቱ ተሳታፊዎች መካከል፣ የኢዜማ ምክትል መሪ አርክቴክት ዮሐንስ መኰንንና የኢሕአፓ ዋና ጸሐፊ ደስታ ጥላሁን፣ ተሰብሳቢዎች ስላነሧቸው ጥያቄዎች እና ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለሰጧቸው ምላሾች ተናግረዋል፤ ውይይቱ መልካም እንደነበረም ገልጸዋል፡፡

የውይይቱን ጥሪ ካልተቀበሉ ፓርቲዎች አንዱ የኾነው የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ሊቀ መንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና፣ ያልተሳተፍነው “ገዢው ፓርቲ ችግሮችን ለመፍታት የፖለቲካ ፍላጎት ስለሌለው ነው፤” ብለዋል፡፡ መንግሥት ውይይቱን የሚፈልገው ''ለፎቶ ነው'' ሲሉም ተችተዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።