የፕሪቶርያው ስምምነት ግልጽነት እንደሚጎድለው የተቹ ተቃዋሚዎች “ለቀጣይ ግጭት በር ይከፍታል” አሉ

Your browser doesn’t support HTML5

የፕሪቶርያው ስምምነት ግልጽነት እንደሚጎድለው የተቹ ተቃዋሚዎች “ለቀጣይ ግጭት በር ይከፍታል” አሉ

የፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት አተገባበር፣ ግልጽነት የጎደለው እንደኾነ የገለጹ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ “ኢትዮጵያን ዋጋ እያስከፈላት ነው፤” አሉ፡፡

የስምምነቱን የአንድ ዓመት ቆይታ አስመልክቶ፣ የኢሶዴታ ሊቀ መንበር ዶር. ራሄል ባፌ እና የኢዜማ የድርጅት ጉዳዮች ሓላፊ ዋሲሁን ተስፋዬ፣ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት አስተያየት፣ የስምምነቱ የግልጽነት እና የአፈጻጸም ውስንነት፣ በዐማራ ክልል ለተፈጠረው ግጭትም አንዱ መንሥኤ እንደኾነ አስረድተዋል፡፡

እነኚኽ፣ ከስምምነቱ አፈጻጸም ጋራ የተያያዙ ናቸው ያሏቸው ግልጽነት የጎደላቸው አካሔዶች ካልተቀረፉ፣ ለቀጣይ ግጭቶችም በር ሊከፍቱ እንደሚችሉ፣ የፓርቲዎቹ አመራሮች ስጋታቸውን አመልክተዋል፡፡

ስምምነቱ የተፈጻሚነት ጉድለት እንዳለው፣ ህወሓት በተደጋጋሚ ሲገልጽ፤ የኢትዮጵያ መንግሥት በበኩሉ፣ ይህን አስመልክቶ ስለሚነሡ ቅሬታዎች ብዙም ምላሽ ሲሰጥ አይስተዋልም፡፡

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡