የኦፌኮ አመራር አባላት የመከላከያ ምስክሮቻቸውን ማሰማት ጀመሩ

  • መለስካቸው አምሃ

አቶ በቀለ ገርባ /ፎቶ ሶሻል ሚዲያ/

አራቱ የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግሬስ አመራር አባላትን ጨምሮ የቀረበባቸውን ክስ እንዲከላከሉ፣ የተበየነባቸው ተጠርጣሪዎች የመከላከያ ምስክሮቻቸውን ማሰማት ጀመሩ፡፡

አራቱ የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግሬስ አመራር አባላትን ጨምሮ የቀረበባቸውን ክስ እንዲከላከሉ፣ የተበየነባቸው ተጠርጣሪዎች የመከላከያ ምስክሮቻቸውን ማሰማት ጀመሩ፡፡

አቶ በቀለ ገርባ ለፍርድ ቤቱ በሰጡት ቃል፣ ሥልጣንን ከሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት ውጭ ለመያዝ ፍላጎትም ምኞትም ኖሮዋቸው እንደማያውቅ ተናገሩ፡፡

“እነ ጉርሜሳ አየኖ” በሚል መዝገብ ዓቃቤ ሕግ ከአመት በፊት ክስ ያቀረበባቸው አሥራ ሰባት ተጠርጣሪዎች፣ የመከላከያ ምስክሮቻቸውን ቃል፣ ማሰማት ጀመሩ፡፡

በተለይም ከትናንት አንስቶ አራቱም የኦፌኮ አመራር አባላት አቶ ጉርሜሳ አያኖ፣ አቶ ደጀኔ ጣፋ፣ አቶ አዲሱ ቡላላ እና አቶ በቀለ ገርባ ሕጉ በሚፈቅደው መሰረት የየግላቸውን የተከሳሽነት ቃል፣ ለፍርድ ቤቱ ሰጥተዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

የኦፌኮ አመራር አባላት የመከላከያ ምስክሮቻቸውን ማሰማት ጀመሩ