ዶ/ር መረራ ጉዲና፣ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ፣ ጃዋር መሐመድና ሌሎች ተከሰሱ

  • መለስካቸው አምሃ
ፌደራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ሕገ መንግሥቱንና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል ለማስወገድ ሙከራ አድርገዋል በሚልና ከአስቸኳይ ጊዜ ዓዋጁ ርምጃዎች ጋራ የተያያዙ ግዴታዎችን በመተላለፍ ወንጀል በዶ/ር መረራ ጉዲና ላይ ክስ መሠረተ። ከእርሳቸው ጋርም በዶ/ር ብርሃኑ ነጋና በጀዋር መሐመድ ላይም ተመሣሣይ ክስ መሥርቷል።

ፌደራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ሕገ መንግሥቱንና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል ለማስወገድ ሙከራ አድርገዋል በሚልና ከአስቸኳይ ጊዜ ዓዋጁ ርምጃዎች ጋራ የተያያዙ ግዴታዎችን በመተላለፍ ወንጀል በዶ/ር መረራ ጉዲና ላይ ክስ መሠረተ። ከእርሳቸው ጋርም በዶ/ር ብርሃኑ ነጋና በጀዋር መሐመድ ላይም ተመሣሣይ ክስ መሥርቷል።

ኢሳት ወይንም ኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥንን እና የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ የተባሉ ድርጅቶችን ደግሞ በሽብር ወንጀል ከሷቸዋል፡፡

ከዓቃቤ ሕግ የክስ ማመልከቻ ለማስተዋል እንደሚቻለው ዶ/ር መረራ ጉዲና፣ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ እና ጃዋር መሐመድ በ1996ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ሕግ የተለያዩ ድንጋጌዎችን በመጣስ፣ የአድማ ስምምነት በማድረግ ሽብርና ሁከት በሀገር ውስጥ እንዲቀጥል፣ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ባልሆኑ ተቋማት ንብረት እንዲወድም ሕገ መንግሥቱንና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል ለማስወገድ ሁከትና ብጥብጥ እንዲፈጠር በተፈጠረው ሁከትና ብጥብጥ አመራር በመስጠት የተሳተፉ በመሆኑ በዋና ወንጀል አድራጊነት በፈፀሙት በሕገ መንግሥቱና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል ለማስወገድ ሙከራ ወንጀል ተከሰዋል ይላል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ፣ ጃዋር መሐመድና ሌሎች ተከሰሱ