የችሎት ዘገባ

የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፖርቲ ሊቀመንበር አቶ እስክንድር ነጋና ሌሎች ሦስት ተከሳሾች ያቀረቡት የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ተደረገ። አምስተኛ ተከሳሽ በ30 ሺህ ብር ዋስ እንዲፈቱ ተወሰነላቸው። ፍርድ ቤቱ ልዩ ልዩ ትዛዞችን ሰጥቶ በተከሳሾች የመጀመሪያ ደረጃ የክስ መቃወሚያ ብይን ለመስጠት ቀጠሮ ቆርጧል።

በሌላም በኩል ሁለት ሌሎች ተከሳሾች የደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ህገ መንግሥታዊ ሥርዓት ንደዋል፤ ከባድ የሙስና ወንጀል ፈፅመዋል ተብለው በተጠረጠሩ በስድስት የወላይታ ዞን ከፍተኛ አመራሮች እና ፖሊቲከኞች በወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተፈቅዶ የነበረውን የዋስትና መብት አገደ።

ፍርድ ቤቱ ዛሬ በሃዋሳ ከተማ ባስቻለው ችሎት የወላይታ ዞኑ አስተዳዳሪ የነበሩትን አቶ ዳጋቶ ኩንቤን ጨምሮ ፍርድ ቤት የቀረቡ ስድስት ተጠርጣሪዎች ፍርድ ቤት በቀረቡበት ማረሚያ እንዲገቡ ትዕዛዝ የሰጠ ሲሆን ለመስከረም 21/2013 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ

Your browser doesn’t support HTML5

የችሎት ዘገባ