ኦብነግ "ትጥቅ ፈትቶ" ተቀላቅሏል

የኢትዮጵያ መንግሥትና የኦብነግ መሪዎች - /ፎቶ ፋይል፤ አሥመራ ጥቅምት 11/2011 ዓ.ም./

የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃ አውጭ ግንባር /ኦብነግ/ ወደ ሰላማዊ ትግል መግባቱን ያሳወቀው ትጥቁን ፈትቶ መሆኑን ቃል አቀባዩ አቶ ሃሰን አብዱላሂ ለቪኦኤ ተናግረዋል።

የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃ አውጭ ግንባር /ኦብነግ/ ወደ ሰላማዊ ትግል መግባቱን ያሳወቀው ትጥቁን ፈትቶ መሆኑን ቃል አቀባዩ አቶ ሃሰን አብዱላሂ ለቪኦኤ ተናግረዋል።

ታጣቂ የነበሩ አባላቱ ወደ ኅብረተሰቡ የሚቀላቀሉባቸውን ሁኔታዎች ለማመቻቸት የሚሠሩ ኮሚቴዎችም መቋቋማቸውን ገልፀዋል።

የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃነት ግንባር ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ሲታገል መቆየቱን አቶ ሃሰን አመልክተው በኢትዮጵያዊነት ጉዳይ ላይ “የሚወስነው ሕዝቡ ነው” ብለዋል።

የኦብነግ መሪዎች ከዚያድ ባሬና እሥላማዊ ፍርድ ቤቶችን ከመሣሰሉ ከሌሎችም ፀረ-ኢትዮጵያ ኃይሎች ጋር ወግኖ የኖረ፣ ኢትዮጵያን የወጋ ነው ተብሎ የተሰማበትን ክስም አቶ ሃሰን አስተባብለዋል።

ለቃለ-ምልልሱ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

ኦብነግ ትጥቅ ፈትቶ ተቀላቅሏል