የተናጥል ተኩስ አቁም ማድረጉን ያስታወቀው የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አውጪ ግንባር /ኦብነግ/ አመራሮች ትላንት ማምሻውን አዲስ አበባ ገብተዋል።
አዲስ አበባ —
የተናጥል ተኩስ አቁም ማድረጉን ያስታወቀው የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አውጪ ግንባር ኦብነግ አመራሮች ትላንት ማምሻውን አዲስ አበባ ገብተዋል።
ወደ ሃገር ውስጥ ገብተው በሰላማዊ መንገድ ለመታገል የወሰኑት ዶ/ር አብይ አሕመድ ወደ ስልጣን ከመጡ በኃላ በርካታ ለውጦች እየታዩ በመሆናቸው እንደሆነ የድርጅቱ ቃል አቀባይ ገልፀዋል።
“ሻንጣችንን ይዘን ነው የመጣነው አንመለስም” ሲሉም ተናግረዋል። የኦብነግ ውሳኔ ለተጀመረው የለውጥ ጉዞ ትልቅ አስተዋፆ ያበረክታል ያሉት ደግሞ የመንግስት ኮሚውኒኬሽን ፅ/ቤት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ካሳሁን ጎፌ ናቸው።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5