ቄስ ኦሞት አግዋ በዋስ ተለቀዋል

የዓለም ባንክ አስተርጓሚና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ቄስ ኦሞት አግዋ የቀረበባቸው የሽብር ሕግ ወደ መደበኛ የወንጀል ሕግ ተቀይሮ በይግባኝ በ50 ሺህ ብር ዋስ ከእስር ተለቀቁ። ከሀገር እንዳይወጡም ታግደዋል።

ፍርድ ቤቱ ይህን ውሳኔ የሰጠው ጥር 10/2009 ዓ.ም ቢሆንም የዋስትናው ገንዘብ ከተያዘ በኋላ አፈፃፀሙ የሰባት ቀናት ጊዜ ወስዶ ትናንት ጥር 17/2009 ዓ.ም ከእስር ተለቀዋል።

ቄስ ኦሞት አግዋ በጋምቤላ የመካነ እየሱስ ቤተክርስቲያን ቄስ ናቸው። የዓለም ባንክ የቁጥጥር ቡድን በጋምቤላ ተፈጽሟል የተባለውን የኢንቨስትመንት በደሎችን ለመመርመር በክልሉ ሲነቀሳቀስ በአስተርጓሚነት እና በመንገድ መሪነት ይሰሩ እንደነበር ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ሂዩማን ራይትስ ወች ስለ ቄስ ኦሞት አግዋ ባወጣው ሪፖርቱ ይገልፃል።

ቄስ ኦሞት የቀረበባቸው የሽብር ሕግ ወደ መደበኛ የወንጀል ሕግ ተቀይሮ በይግባኝ በ50 ሺህ ብር ዋስ ከእስር ተለቀቁ። ከሀገር እንዳይወጡም ታግደዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

ቄስ ኦሞት አግዋ በዋስ ተለቀዋል