ምሥራቅ ወለጋ ውስጥ የተጠለፉ ሰዎችን የማስለቀቅ ጥረት

አቶ ኃይሉ አዱኛ

ሰሞኑን ምሥራቅ ወለጋ አካባቢ ባለሥልጣናቱ ሸኔ ብለው በሚጠሯቸው ታጣቂዎች ታግተዋል የተባሉ ስድስት ሰዎችን ለማስለቀቅ መንግሥት የሚቻለውን ሁሉ እንደሚያደርግ የኦሮምያ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ ለቪኦኤ ገልፀዋል።

በአባ ገዳዎች ጥሪ ከ300 በላይ ወጣቶች እራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ብሎ ከሚጠራው ቡድን ወጥተው እጃቸውን መስጠታቸውንም ኃላፊው አስታውቀዋል።

ታጣቂው ቡድን ከባለሥልጣናቱ የሚሠነዘሩበትን ክሦች በተደጋጋሚ ሲያስተባብል ቆይቷል።

ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

ምሥራቅ ወለጋ ውስጥ የተጠለፉ ሰዎችን የማስለቀቅ ጥረት