በኦሮሞ ነፃነት ግንባር እና በኢትዮጵያ መንግሥት መካከል የተዋቀረው የአባ ገዳዎች እና ሽማግሌዎች የዕርቅ ሂደት የቴክኒክ ኮሚቴ፣ የዕርቅ ሂደቱ ተስፋ ሰጪ መሆኑን እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋርም ውይይት መደረጉን ገለፀ።
አዲስ አበባ —
በኦሮሞ ነፃነት ግንባር እና በኢትዮጵያ መንግሥት መካከል የተዋቀረው የአባ ገዳዎች እና ሽማግሌዎች የዕርቅ ሂደት የቴክኒክ ኮሚቴ፣ የዕርቅ ሂደቱ ተስፋ ሰጪ መሆኑን እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋርም ውይይት መደረጉን ገለፀ።
በሰላም ሥምምነቱ የተኩስ እና ግጭት ማቆም ሥምምነት ቢደርስም ሰዎች በተለያዩ ቦታዎች እየሞቱ የተጠየቁት አቶ ጀዋር እና አቶ በቀለ፣ ችግሩን ተከትሎ ከሁለቱም ወገን ስሞታ እየቀረበ እና ሕዝቡም ስለ ችግሩ እየተናገረ ነው፣ ለመፍትሔው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየተወያየን ነው ብለዋል።
ቴክኒክ ኮሚቴውን በመወከል ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ የሰጡት የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ ስራ አስኪያጅ ጃዋር መሐመድ እና የኦፌኮ ዋና ፀኃፊ አቶ በቀለ ገርባ፣ የቴክኒክ ኮሚቴው በስምንት ቡድን በመከፋፈል ለውሳኔው ተግባራነት ወደ ተለያዩ አካባቢዎች ይሰማራል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5
Your browser doesn’t support HTML5