የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በዓለም ዙሪያ በሠላሳ ሦስት ሃገሮች በከባድ ሠብዓዊ ችግር ላለ ወደዘጠና ሦስት ሚሊዮን የሚጠጋ ህዝብ የ22.2 ቢሊዮን ዶላር ተማፀነ፤ ይህ ከምንጊዜውም ግዙፍ የነፍስ አድን እርዳታ ተማፅኖ መሆኑ ታውቁዋል።
ዋሺንግተን ዲሲ —
በዓለማችን ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ ባልታየ መልኩ የገዘፈ ሠብዓዊ ቀውስ መደቀኑን ነው የተባባሩት መንግሥታት ድርጅት የገለጠው።
ከአንድ መቶ ሃያ ስምንት ሚሊዮን በላይ ህዝብ በግጭት ከመኖሪያው በመፈናቀል በተፈጥሮ አደጋ ለከባድ ችግር ተጋልጠዋል፤ አስቸኳይ ርዳታ ያስፈልጋቸዋል ብሉዋል።
ከመቶ ሃያ ስምንቱ ሚሊዮኑ ውስጥ ዘጠና ሦስት ሚሊዮን ገደማ የሚሆነው ሕዝብ አጣዳፊ ሕይወት አድን ርዳታ እንደሚያስፈልገው የመንግሥታቱ ድርጅት አስታውቁዋል።
ሊሳ ሽላይን ያጠናቀረችውን ዘገባ ቆንጂት ታየ ታቀርባለች፡፡
ለሙሉው ዘገባ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
Your browser doesn’t support HTML5
ተመድ በዓለም ዙሪያ ለሠላሳ ሦስት ሃገሮች የገንዘብ ድጋፍ ጠየቀ