የፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ የመጨረሻ የውጭ ፕሬዚዳንታዊ ጉብኝት

ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ እና የግሪክ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሌክሲስ ሲፕራስ

ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በአውሮፓና በደቡብ አሜሪካ በሚያደርጉት ጉዞ ተመራጩ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኔቶን ጨምሮ ከመላው ዓለም መሪዎች ጋር ግንኙነታቸውን ለመቀጠል እንደሚሹ መልዕክት መያዛቸውን ገለፁ።

ኦባማ በጀርመን፣ በግሪክና በፔሩ በሚያደሩት የውጭ ሀገር ጉብኝት ከዓለም መሪዎች ጋር እንደሚገናኙ ታውቋል።

ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በሥልጣን ዘመናቸው የመጨረሻ ጉብኝት ከአደረጉባቸው የአውሮፓ ሀገሮች የመጀመሪያዋ ግሪክ ስትሆን ባለሥልጣኖቿ ዛሬ ማክሰኞ አቴንስ ውስጥ ከፍተኛ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ከዚያም ከጠቅላይ ሚኒስትሩ አሌክሲስ ሲፕራስ ጋር ተገናኝተው ስለ ቀጣይ ስላለው የኢኮኖሚ ግኙነት ተወያይተዋል።

ኦባማ የዴሞክራሲ የትውልድ ሀገር በሆነችው ግሪክ የተደረገላቸው አቀባበል አስደሳች መሆኑን ገልፀው አመስግነዋል።

የግሪክ መንግሥት ለአፍሪካና ለመካከለኛው ምሥራቅ ፍልሠተኞች በሩን በመክፈት ያደረጉትን አስተዋፅዖ በማውሳት በአጠቃላይ የስደተኞችን ቀውስ በማርገብ የተደረገውን እገዛ ጠቅሰው አመስግነዋል።

ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በግሪክ

​ፕሬዚዳንት ኦባማና የግሪኩ ጠቅላይ ሚኒስትር አሌክሲስ ከውይይታቸው በኋላ የጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጡም ታውቋል።

ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በአውሮፓ በጀመሩት ጉዞ፣ ከተመራጩ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ ተመስርተው ለጋዜጠኞች እንደገለፁት፣ ለዓለም መሪዎች መድረስ ያለበትን የተመጩን ፕሬዚዳንት ወሳኝ መልዕክት ይዘዋል።

ቀጣዩ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ኔቶን ጨምሮ ከዓለሙ መሪዎች ጋር የሚኖረውን ስትራቴጂካዊ ግንኙነት ለመቀጠል ማቀዳቸውን ነው ሚስተር ኦባማ የተናገሩት።

ከዋይት ሀውስ ሜሪ አሊስ የላከችውን ዘገባ አዲሱ አበበ ዝርዝሩን ይዟል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

የፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ የመጨረሻ የውጭ ፕሬዚዳንታዊ ጉብኝት