ፕሬዚዳንት ኦባማ እና ዶናልድ ትራምፕ - ሰለ ፊደል ካስትሮ

ፎቶ ፋይል

በዩናይትድ ስቴትስና በኩባ መካከል ያለው ወዳጅነት ከ50 ዓመታት በኋላ መታደሱ አስደሣች መሆኑን በኩራት የገለፁት ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ በሟቹ የኩባ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ፊደል ካስትሮ ሞት የተሠማቸውንም ሃዘን ዲፕሎማሲያዊ በሆነ መንገድ ለቤተሰባቸው ገልፀዋል።

ተመራጩ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ግን ቀድሞውኑ በዩናይትድ ስቴትስ እና በኩባ መካከል በፕሬዚዳንት ኦባማ የተጀመረውን ዲፕሎማስያዊ ግንኙነት አልወደዱትም፡፡

ፊደል ካስትሮ

የፊደል ካስትሮን ሞት በተመለከተም ነፍሰ ገዳይና አምባገነን በሚል ጠንካራ አስተያየት ነው የገለፁት።

በሁለቱ አገላለፅ ላይ የታየው ልዩነት የቪኦኤዋ ሲንዲ ስቴን እንደዘገበችው፣ ምናልባትም በዋሽንግተን እና በሀቫናን ዲፕሎማሲያዊ ትስስር ላይ ከፍተኛ አንደምታ ሊያሳድር ይችላል።

​ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

ፕሬዚዳንት ኦባማ እና ዶናልድ ትራምፕ - ሰለ ፊደል ካስትሮ