የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ እና የቲቤቱ መንፈሳዊ መሪ ዳላይ ላማ፣ በዓለም ዙሪያ ሰላምን ለማስፈን ስለሚቻልበት ሁኔታ ለመወያየት ዛሬ አርብ ኒው ዴልሂ ውስጥ መገናኘታቸውን፣ የዳላይ ላማ ቢሮ አስታወቀ።
ዋሺንግተን ዲሲ —
የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ እና የቲቤቱ መንፈሳዊ መሪ ዳላይ ላማ፣ በዓለም ዙሪያ ሰላምን ለማስፈን ስለሚቻልበት ሁኔታ ለመወያየት ዛሬ አርብ ኒው ዴልሂ ውስጥ መገናኘታቸውን፣ የዳላይ ላማ ቢሮ አስታወቀ።
ሦስት አገሮችን እየጎበኙ ያሉት ኦባማ፣ ከቻይና በኋላ ሕንድ ሲገቡ፣ ከጠቅላይ ሚኒስትሩናሬንድራ ሞዲ ጋርም ተገናኝተዋል።
ዳላይ ላማ በአንድ የኒው ዴልሂ ውቴል ውስጥ ከሚስተር ኦባማ ጋር በተገናኙበት ወቅት፣
“ከጥንቱ ታማኝ ወዳጅ ጋር ሕብረት ማድረግ ደስ ይላል” ማለታቸው ተሰምቷል።
ሁለቱ ሲገናኙ የአሁኑ ለሥድስተኛ ጊዜ መሆኑም ታውቋል።