የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ ለሃያ አንድ ሰዎች ፕሬዚደንታዊ የነፃነት ሜዳልያ ሸለሙ።
ዋሺንግተን ዲሲ —
ሚስተር ኦባማ ለሀገሪቱን ከፍተኛ ሲቪሎች ለመጨረሻ ጊዜ የሰጡት ሽልማት ነው።
“የነፃነት ሜዳሊያው አሜሪካ ውስጥ ማንኛውም ሰው ሀገሪቱን የተሻለች እንድትሆን ለመርዳት ይችላል የሚለውን ዕምነታችንን የምናከብርበት ነው” ብለዋል - ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ ።
ዛሬ መንፈሳችንን ከፍ ከፍ ያደርጉልንን አንድነታችንን ያጠናከሩልንና ወደ ዕድገት የገፉንን ልዩ የሆኑ አሜሪካውያን እናከብራለን ሲሉ ከተሸላሚዎቹ መካከልም በሲኒማ በሙዚቃ፣ በኪነ ጥብብ፣ በስፖርት፣ በሣይንስ እና የበጎ አድራጎት ሥራዎች ላይ የተሰማሩ ይገኙበታል።
የማይክሮሶፍት ኩባኒያው መስራች ባለቤት ቢል ጌትስና ባለቤታቸው ሜሊንዳ ጌትስ በጎ አድራጎት ድርጅታቸው የጤና ጥበቃ ለድህነት እና ለረሃብ ማስወገጃ እንቅስቃሴዎች ሰላሣ ስድሥት ቢሊዮን ዶላር ለግሰዋል።
ቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ
“ተባብረን ከሰራን ይቺን ዓለም የሚገባት ቦታ እንድትደርስ ለማድረግ እንችላለን በሚለው የተስፋ ስንቃቸው እኛንም እያነቃቁን ናቸው” ብለዋል፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
Your browser doesn’t support HTML5