“እናንት ልታከናውኑት የማይቻላችሁ ኣንዳችም ነገር የለም!!” የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ መልእክት ለኬንያ ወጣቶች።
“በአሜሪካ ፕሬዚደንትነት ወደኬንያ በመምጣት የመጀመሪያ በመሆኔ ኩራት ይሰማኛል። ለነገሩ የመጀመሪያው ኬኒያዊ አሜሪካዊ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንትም ነኝ።"
ከኬንያዊ አባት የተወለዱት ፕሬዚደንት ሙስናን፡ በወገን መሹውሹዋምን እና ጎሰኝነትን የማስወገዱን እርምጃ መቀጠል ኣለባችሁ በማለት ለኬንያ ወጣቶች ጥሪያቸውን አሰምተው ታሪካዊ ጉብኝታቸውን ሲያጠናቅቁ ወጣቶቹ በጋለ ስሜት ተቀብለዋቸዋል።
ፕሬዚደንት ኦባማ እሁድ እለት በናይሮቢ ሳፋሪኮም ስቴዲየም ለተሰባሰቡ አራት ሺህ ተማሪዎች ባደረጉት ንግግር “የዚህ ጉዞ መሰረት የሚሆነው ግን ከሙስና የጸዳ፡ ተቃራኒ ድምጾችን እና አንድነትን የሚያከብር ህብረተሰብ ሲኖር ነው” ብለዋል።
“አንድ በጣም ግልጽ ላደርግ የምሻው በጎሳ በዘር ብቻ የተመሰረተ ፖለቲካ አገርን እንደሚበታተን ነው። ውጤቱ ውድቀት ነው” ብለዋል የአሜሪካው ፕሬዚደንት።
Your browser doesn’t support HTML5