የዩናትድ ስቴትስ (United States) ፕረዚዳንት ባራክ ኦባማ እስላማዊ መንግስት ነኝ የሚለውን ጽንፈኛ ቡድንን የሚቃወሙት ሁሉ “ያሸንፋሉ” ብለዋል።
የፕረዚዳንትነት ስልጣናቸው እስከሚያበቅዝበት ጊዜ ድረስም “የማይናቅ መሻሳል” ይኖራል የሚል እምነት እንዳላቸው ጠቁመዋል።
ፕረዚዳንት ኦባማ NPR ከተባለው ዋናው መሰረቱ ዋሽንግተን ዲሲ ካከሆነው ሬድዮ ጣብያ ጋር ባደረጉት ቃለ-መጠይቅ እስላማዊ መንግስት ነኝ የሚለው ቡድን “ከይሲ ድርጅት” ነው ብለዋል። ነገር ግን ይህ ቡድን በዩናትድ ስቴትስ (United States) ላይ ሊያደርስ የሚችለው የከፋ ጉዳት ሰዎች በሱ ምክንያት የኑሮ ዘየቸውንና እሴታቸውን ከለወጡ ነው በማለት ጫና ሰጥተዋል።
ፕረዚዳንቱ አያይዘውም ይህ ዩናትድ ስቴትስ (United States) ን ሊያጠፋ የሚችል ድርጅት አይደለም። አደጋ ላይ ሊጥለን የሚችል ግዙፍ የኢንዱስትሪ ሀይልም አይደለም። ነገር ግን ህዝባችንንና ቤተሰባችንን ሊጎዳ ይችላል። ስለሆነም ሰው ለምን እንደሚሰጋ እራዳለሁ ብለዋል።
ፕረዚዳንት ኦባማ በኢራቃና በሶርያ ባሉት የቡዱኑ አማጽያን ላይ በዩናትድ ስቴትስ (United States) የሚመራ የጥምረት ሃይል የአየር ድንደባ እንዲካሄድ ከፈቀዱ ከአንድ አመት በላይ ሆኗል። ከዚያን ጊዜ አንስቶ 9,000 የአየር ድብደባዎች ተካሄደዋል። ጽንፈኛው ቡድን ይቆጣጠራቸው ከነበሩት ቦታዎች 40 ከመቶዎቹን አጥቷል ሲሉ ፕረዚዳንቱ ተናግረዋል።
ያም ሆኖ ግን ቡድኑ አሁንም በሶርየና በኢራቅ ያሉ አበይት ከተማዎችን ሳይቀር ሰፊ ቦታዎችን መቆጣጠሩ አልቀረም። ይህ ሁኔታም በዩናትድ ስቴትስ (United States) ላይ ነቀፊታ አስከትሏል። የአሜሪካ ወታደሮች እንዲላኩም ጥሪ እየተደረገ ነው። ዘገባውን ከተያያዘው የድምጽ ፋይ በመጫን ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5