የመንግስታቱ ድርጅትና ፕሬዝደንት ኦባማ ሁከተኛ ጽንፈኝነትን በማስወገድ ዙሪያ ተወያዩ

ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት 70ኛ ጉባዔ ጎን በሁከተኛ ጽንፈኝነትና በሽብር ፈጠራ ላይ በተካሄደው ስብሰባ

Your browser doesn’t support HTML5

የመንግስታቱ ድርጅትና የዓለም መሪዎች ሁከተኛ ጽንፈኝነትን በማስወገድ ዙሪያ ያደረጉት ውይይት


በተባበሩት መንግስታት ድርጅት 70ኛ ጉባዔ ጎን ትናንት ማክሰኞ በሁከተኛ ጽንፈኝነትና በሽብር ፈጠራ ላይ በተካሄደው ስብሰባ ላይ ISIL ወጣቶችን የማጋጋልና የመመልመል አቅም እንዳይኖረው ማድረግ እንደሚገባ፤ ስብሰባውን የመሩት የዩናይትድ ስቴይትስ ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ አሳስበዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ የተመልማዩ ብዛት በከፍተኛ ቁጥር ማሻቀብ አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱን የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ጸሃፊ ባን ኪ ሙን ተናግረዋል።

“በሴቶችና በልጃገረዶች ላይ ርህራሄ የለሽ ጭካኔ ይፈጽማሉ። የሰላምን የፍትህና የሰብዓዊ ክብርን ዓለም አቀፍ እሴቶች ይጻረራሉ።”

እስላማዊ መንግስት ነኝ የሚለውን ቡድን የመሳሰሉ ሁከተኛ ጽንፈኝነትን የሚያራምዱ ቡድኖችን ለማሸነፍ የተባበረ ምላሽ መስጠት እንደሚገባ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ ባን ኪ ሙን እየጎተጎቱ ነው።

“በአንድ ሌሊት የማይጠፋ ግን ልናሸንፈው የምንችለው ችግር ነው። አሳታፊ ህብረተሰብን በመፍጠር ሰው ክብር ያለውን ኑሮ እንዲኖር በማስቻልና ይህንን እጅግ ጠቃሚ የሆነ ጉዞ ዘወትር በመንግስታቱ ድርጅት ቻርተርና በሰብዓዊ መብቶች ዓለም አቀፍ ድንጋጌዎች እየተመራን በማሳካት ልንጋፈጠው እንችላለን።” ብለዋል ባን ኪ ሙን።

የናይጀሪያው ፕሬዝደንት ሙሀመዱ ቡሃሪ

የዩናይትድ ስቴይትሱ ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ ISILን በውጊያ ግንባር ማሸነፍ በቂ አይሆንም ብለዋል ፕሬዝደንት ኦባማ የሁከተኛ ጽንፈኝነትን ለመከላከል የተጠራውን ጉባዔ ሲከፍቱ።

“ሲጀመርም ወጣቶችን እንዳያነሳሳና እንዳያቀጣጥል ሌሎችንም ለአመጽ መቀስቀስ እንዳይችል ነው ማድረግ ያለብን።”

ፕሬዝደንት ኦባማ አክለውም “አስተሳሰቦችን በጠመንጃ ማሸነፍ አይቻልም። አስተሳሰቦች የሚሸነፉት፤ ከነርሱ በሚበልጡና በሚሻሉ አስተሳሰቦች ነው። ይበልጥ ሳቢ በሆኑና ሊያነቃቁ በሚችሉ አስተሳሰቦች ነው" ብልዋል

ህብሩ የበዛ፤ ታጋሽ፣ ሁሉን አሳታፊ የሆነ ህብረተሰብ ለመገንባት እራሳችንን አስገዝተን መስራት አለብን ሲሉ ሚስተር ኦባማ አሳስበዋል።

“እንዲህ ዓይነቱን ህብረተሰብ ጽንፈኞቹ ዘወትር የሚፈልጉትንና ሌሎችን ለማጥመድ የሚጠቀሙባቸውን፤ ጸረ-ሙስሊምና ጸረ ፍልሰተኛ ወይንም መጤ ጠል የሆኑ መከፋፈልን፤ ፍርሃትን፤ ቂምን የሚዘሩ የክፋት አድራጎቶችን ከውስጡ ማስወገድ የሚችል ነው።”

የመሪዎችን ትኩረት የሳበው ጉባዔ

በዋይት ሃይውስ ቤተመንግስት ሁከተኛ ጽንፈኝነት ላይ የተካሄደ የምክክር ስብሰባ በየካቲት ወር በፕሬዝደንት ኦባማ ጥሪ የተካሄደ ሲሆን በኒው ዮርኩ ጉባዔ ከመቶ በላይ ሀገሮች በዚህ ጉባኤ ላይ ተገኝተዋል። የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኋይለማርያም ደሳለኝም ነዚህ ጉባዔ ላይ ተካፍለዋል። ከ120 በላይ የሚሆኑ የሲቪል ማህበራት መሪዎችና የግሉ ዘርፍም ተካፍለዋል።