በሰሜን ሸዋ የመስጅድ ኢማም ታግተዉ መገደላቸው ተነገረ

የኢትዮጵያ ካርታ

Your browser doesn’t support HTML5

በሰሜን ሸዋ የመስጅድ ኢማም ታግተዉ መገደላቸው ተነገረ

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ ከሳምንታት በፊት በታጣቂዎች ታግተው ነበር የተባሉ የኃይማኖት አባት መገደላቸው ተነገረ።

በሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ አረቦ መስጅድ ኢማም ኾነው ሲያገለግሉ ነበሩ የተባሉት ሼክ መከዬ ሰይድ ለሳምንታት ታግተዉ ከተወሰዱ በኋላ ባለፈው ሳምንት ሐሙስ አስከሬናቸው መምጣቱንና ሥርዓተ ቀብራቸው መፈፀሙ ተነግሯል። የደራ ወረዳ አስተዳደር ድርጊቱ መፈፀሙን አረጋግጧል። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽንም ስለግድያዉ መረጃ እንደደረሰዉ አስታውቋል።

የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎች አማካሪ መኾናቸውን የተናገሩት ጅሬኛ ጉደታ፣ ታጣቂዎቻቸው ጥቃቱን እንዳልፈጸሙ ተናግረዋል።