የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሰሜን ኮርያ የምትደቀነውን አደጋ በሚመለከት “መልሱ መናገር አይደለም” ብለዋል። ፕሬዚዳንቱ ይህን ያሉት ሰሜን ኮርያ ተጨማሪ ቦሊስቲክ ሚሳይል ለፍተሻ ከተኮሰች በኋላ ነው።
ዋሺንግተን ዲሲ —
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሰሜን ኮርያ የምትደቀነውን አደጋ በሚመለከት “መልሱ መናገር አይደለም” ብለዋል። ፕሬዚዳንቱ ይህን ያሉት ሰሜን ኮርያ ተጨማሪ ቦሊስቲክ ሚሳይል ለፍተሻ ከተኮሰች በኋላ ነው።
“ዩናይትድ ስቴትስ ለ25 ዓመታት ያህል ከሰሜን ኮርያ ጋር ስትነጋገርና የማባበያ ገንዘብ ስትከፍል ቆይታለች። “መልሱ መነጋገር አይደለም” ሲሉ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ዛሬ ማለዳ የትዊተር መልእክት አስተላልፈዋል።
ሰሜን ኮርያ በበኩልዋ በጃፓን ላይ ተምዘግዛጊ ሚሳይሎችን እንደተኮሰች አማና፣ በመቀበል በአሁኑ ወቅት ደቡብ ኮርያና ዩናይትድ ስቴትስ በሕብረት ለሚያካሄዱት ወታደራዊ ልምምድ ምላሽ ነው ብላለች።