የሰሜን ኮሪያውን መሪ ኪም ጆንግ ኡን ሌላ የሃይድሮጂን ቦምብ ፓሲፊክ ውቅያኖስ ላይ እንደሚሞክሩ ይፋ ካደረጉ በኋላ፣ የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ደግሞ “እብድ” ሲሉ እንደተናገሯቸው ተሰማ።
ዋሺንግተን ዲሲ —
የሰሜን ኮሪያውን መሪ ኪም ጆንግ ኡን ሌላ የሃይድሮጂን ቦምብ ፓሲፊክ ውቅያኖስ ላይ እንደሚሞክሩ ይፋ ካደረጉ በኋላ፣ የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ደግሞ “እብድ” ሲሉ እንደተናገሯቸው ተሰማ።
የኮሪያው መሪ ሙከራውን እንደሚያደርጉ ያስታወቁት፣ ለፕሬዚደንት ትራምፕ ዛቻና የማዕቀብ ማስፈራሪያ ተመጣጣኝ የሆነ እርምጃ እንደሚወስዱ ካሳወቁ በኋላ መሆኑ ነው።
ፕሬዚደንት ትራምፕ ለሰሜን ኰሪያው የኑክሊየር ዛቻ በዛሬው ቀን በሰጡት መልስ፣
"ሕዝባቸውን ማስር፣ ማስራብና መግደል ቁብ የማይሰጣቸው እኒህ ያበዱ ሰውዬ፣ ታይቶ በማይታወቅ ቅጣት ዋጋችውን ያገኛሉ” ብለዋል።
ኪም፣ ፕሬዚደንት ትራምፕን፣ “ቀውስ” ማለታቸው አይዘነጋም።