ሰሜን ኮሪያ በአንድ ወር ውስጥ ሦስተኛውን የኒኩሌየር ሙከራ አካሄደች

  • ቪኦኤ ዜና
የኒኩሌየር ሚሳኤል ሙከራ በቴሌቪዝን ሲከታተሉ

የኒኩሌየር ሚሳኤል ሙከራ በቴሌቪዝን ሲከታተሉ

ሰሜን ኮሪያ በአንድ ወር ውስጥ ሦስተኛውን የኒኩሌየር ሚሳኤል ሙከራ በዛሬው እለት አድርጋለች፡፡

ሙከራው የተካሄደው የሰሜን ኮሪያ አምባሳደር የደቡብ ኮሪያን ጠብ አጫሪነት በመግለጽ በተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ ፊት ንግግራቸውን ከማሰማታቸው ጥቂት ደቂቃዎች በፊት ነው፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ ሙከራውን በማውገዝ “በርካታዎቹን የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት ውሳኔዎችን የሚጥስ ነው ብላለች፡፡

በሰሜን ኮሪያ አጎራባች ለሚገኙ አገሮችም ሆነ ለዓለም አለም አቀፉ ማኅበረሰ ሥጋት መሆኑንም ገልጻለች፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ በዛሬው እለት በሰጡት መግለጫ ከሰሜን ኮሪያ ጋር ለመነጋገር የምናደርገውን ዲፕሎማሲያዊ ጥረት አሁንም እንቀጥልበታለን” ካሉ በኋላ የደቡብ ኮሪያ ሪፐብሊክና ጃፓንን ከጥቃት ለመከላከል ያለንን ቁርጥኝነትም እንደ ብረት የጠነከረ ሆኖ ይቀጥላል ብለዋል፡፡