ሰሜን ኮርያ የቦልስቲክ ሚሳይሎች ተኮሰች

  • ቪኦኤ ዜና
ሰሜን ኮርያ ዛሬ ማለዳ ላይ በአዲስ መልክ የቦልስቲክ ሚሳይሎች ዙር ተኩሳ ባህር ላይ አርፏል።

በያዝነው ሳምንት ለጀምረው የዩናይት ስቴትስና የደቡብ ኮርያ ወታደራዊ ልምምድ ምላሽ “አዲስ ጎዳና” ልወስድ እችላለሁ ስትልም ሰሜን ኮርያ አስጠንቅቃለች።

ሰሜን ኮርያ ሁለት የአጭር ርቀት ቦልስቲክ ሚሳይሎችን የተኮሰችው ከደቡብ ሁዋንግሃይ ከፍለ ሀገር መሆኑን የደቡብ ኮርያ ኤታ ማዦር ሹም ባወጡት መግለጫ ጠቁመዋል። ሚሳይሎቹ 450 ኪሎሜትር በሚሆን ርቀት ተምዘግዝገው ወደ 37 ኪሎ ሜትር ከፍታ መድረሳቸውን ገልጸዋል።

ሰሜን ኮርያ ከሁለት ሳምንታት ባነሰ ጊዜ ውስጥ አራት ዙር የአጭር ርቀት መች ቦልስቲክ ሚስይሎችን አምጥቃለች።